Friday, August 31, 2012

ሐዘን የሸሸገው ፈገግታ




ሐዘን አጥንት ሲደርስ ደግ አይደለም:: ሰውም እግዜሩም አይወዱትም:: ለአገርም አይጠቅምም ለጠላትም ደስ አይበለው:: እንዲህ አገር ነቅሎ ሙሾውን ሲያስነካው ተዉ እሚል ይጥፋ? ምስኪን ትዝ አለኝ... ጃንሜዳ ጋር ሞቶ እሚቀብረው ሲያጣ አዝኖ ወደቤቱ የተመለሰው ሃሃሃሃ…:: ለማንኛውም ሕገ መንግስቱ እንደሚለው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲያርፍ ወይም በሞት ሲለይ አንድ ቀን ብሔራዊ ሃዘን ይታወጃል:: እንደ በረከት ስምኦን ቢሮ አሥራ አራት ቀን መሆኑ ነው:: [በየቀኑ የሚጣስን ሕገመንግስት አንስቶ መከራከሩ ፅንፈኛ ያስብለኛል ስለዚህ ይለፈኝ] በዛ ላይ ዋሽንት አለ [ለአንዳንዶች vuvusela ሆኖባቸዋል]:: ስለዚህም እንደ አንድ ሐዘናችንን ለማስረሳት እንደሚጥር ልማታዊ አፅናኝ በለቅሶው አካባቢ ከተሰሙት ንግግሮች ጀምሮ ወሬው እንዳመራን ውል አልባ ጨዋታ ብንጨዋወትስ...

ሰሞኑን እንደ ጆሮ ስቃዩን ያየ (ሰደቃውን የበላ) የለም... ጆሮ ሆይ አድናቂህ ነኝ!

የልማታዊው በረንዳ አዳሪ አስተያየት፣ "አባታችንን ተማምነን ነው በረንዳ የምናድረው" የሚለው አስገራሚ ለቅሶ የልማታዊውን እስረኛ ሰሜ ባላገሩን ቃለ ምልልስ ያስታውሰናል፤ "በመታሰሬ በጣም ደስተኛ ነኝ መንግስቴንም አመሰግነዋለው" ነበር ያለው ሰሜ ከእስር ቤት እንደወጣ [ሰሜ ሮሚዎን ሆኖ ትያትር እንደተጫወተ ላስታውስ]፡፡ ሰሜን ተንጠላጥለን ወደ ሁዋላ ስንሄድ "ታንክ ተደግፎ መጽሐፍ ያነብ ነበር" ያለው የኢትዮፈርስት ዌብሳይት  አዘጋጅ ቤን፣ "HR 2003 ከማፅደቃቸው በፊት የአሜሪካን ሴናተሮች ጉዳዩን መላልሰው እንዲያዩት የመከሩት የብቸና ገበሬዎችየአሜሪካንን ኢምፔርያሊዝም ከተሳሳተ ርዕዮተ-ዓለሙ እንዲታረም ያስጠነቀቁት የቦረና አርብቶ አደሮች" ...

Tuesday, August 28, 2012

ከመለስ በኋላ!



በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ የፍልሰፍና መምህር እና ከጥቂት የአደባባይ ምሁራን አንዱ የሆነውን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን አነጋግረን  ስለወቅቱ ማሕበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ  ሐሳቦችን ማቅረባችን ይታወሳል፡፡አሁን ደግሞ የአቶ መለስን ‘ድንገተኛ!?’ ሞት  ተከትሎ በድኀረ-መለስ  አትዮጵያና በሌሎች ተያያዥ ጉዳየች ዙሪያ እንደተለመደው ገዢ ሐሳቦቹን ሰጥቶናል፡፡ መልካም ንባብ

የሳምቱ ጋዜጣና መጽሔቶች ከሰኞ እስከ ሰኞ - አሥራሁለት


(ከነሐሴ 14 እስክ ነሐሴ 21/2004)


ሳምንቱ በጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ዜና የተሞላ ነበር፡፡ የሞታቸው ዜና በቲቪ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ምላሾች የተስተናገዱ ሲሆን ጋዜጦች እና ህትመቶችም የዚሁ  አካላት ነበሩ፡፡ የፓትሪያርኩና የጠ/ሚኒስትሩ ህልፈት ዜናዎች እና የሃዘን መግለጫዎች የጋዜጣዎችን ገጾች ያጨናነቁ ነበሩ፡፡

አዲስ ዘመን ጠ/ሚኒስትሩን ሲያስታውስ

በህትመቱ የፓትሪያርኩን ዜና እረፍት ሲያነሳ የነበረው አዲስ ዘመን የጠ/ሚኒስትሩን ሞት በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም "ኢትዮጵያ ታላቁን መሪ በሞት ተነጠቀች ከትላንትና ጀምሮም ብሔራዊ ሃዘን ታውጇል" ብሏል፡፡ በፊት ገጹ ሙሉውን የጠ/ሚኒስትሩን ምስል የያዘው አዲስ ዘመን በተከታታይ ሳምንታዊ እትሞቹ ሙሉውን (ገጽ 3ትን ጨምሮ) ለመለስ ማስታወሻነት እንዲውል አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፕረስ አሰሴሸን፣ ሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝ እና ልማት ባንክ ሃዘናቸውን ለመግለጽ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ አዲስ ዘመን ሳምንቱን ሙሉ የተለያዩ አካላት የሃዘን መግለጫ ሲያስተናግድ ከርሞአል፡፡ "የህዳሴው መሪ" "ለትውልዱ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም" የሚሉ የተለያዩ ጽኁፎችን በፎቶ አጅቦ ያስተናገደው አዲስ ዘመን ምርጥ የጠ/ሚኒስትሩ ንግግሮችን አቅርቦአል፡፡የተወሰኑትን እነሆ፡-

  • የግሌም ሆነ የድርጅቴ አቋም ህገ በመንግስቱ ሊሻሻል የሚችል ምንም አንቀጽ የለውም የሚል ነው፡፡ መለስተኛ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ ይደረግ ቢባል ግን የሚያበሳጭ አይደለም፡፡
  • የመበታተን እና የመበጣጠስ አደጋ ጠፍቶ አሁን የፊዴራሊዝም ስርአት ሰፍኖ የብሄር የብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች መብትና እኩልነት መረጋገጡን ሳይ ደስታ ይሰማኛል፡፡በሃገራችን እየታየ ያለው የልማት እንቅስቃሴ እኛ ብቻ ሳይሆን በውጪ የሚገኙት መንግስታት ለስራም ሆነ ለስብሰባ ሲመጡ ከአመት አመት እየታየ ያለውን ለውጥ በማየት ይገርማቸዋል፡፡
  • ኢትዮጲያ ፌደራሊዝም ስርአቱን የጀመረችው ከቅርብ አመታት ወዲህ በመሆኑ የፊደራል ስርአትን አስቀድመው ከጀመሩ የምትማረው ብዙ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ኢትዮጲያ በስርአቱ ዙሪያ ለተቀሩት ሃገራት የሚተርፍ መልካም ተሞክሮ ያላት ሃገር ሆናለች፡፡

አዲስ ዘመን ከጠ/ሚኒስትሩ ሞት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባለው እትሙ በገጽ ሶስት እትሙ ማህበራዊ ድህረ ገጽ መረጃዎች ተአማኒነት እና አጠቃቀማቸው በሚል ርእስ የማህበራዊ ድህረ ገጾች መረጃዎች ለአመኔታ እንደማይበቁ የሚዳስስ ጽሁፍም አቅርቦ ነበር፡፡

Sunday, August 26, 2012

ከሞቱ ዜና ጋር በተያያ

ማሕሌት ፋንታሁን

የዚህ ጽሑፍ ዋና ቅጂ በኢትዮጵያ እንዳይነበብ በታገደው የዞን ዘጠኝ ጦማር ላይ ይገኛል፡፡
የመለስን ሞት ተከትሎ ብዙ እየተባሉ ያሉ ነገሮች አሉ፡፡ ሬድዮና ቴሌቭዥኑ ሙሉ ሰዓቱን ጠ/ሩ በህይወት ዘመናቸው ያከናወኗቸውን ተግባራት እና ያደረጉትን ንግግር  ሃዘን ውስጥ የመክተት ብቃት ካላቸው ክላሲካል ሙዚቃ እና ዋሽንት ጋር በማቀነባበር በማሰማት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የጠ/ሩን ሞት በተመለከተ በተለያዩ በአገራችን ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎችና ታዋቂ ሰዎች የተሰማቸውን  መሪር ሃዘን እና በምን አይነት ሁኔታ እያዘኑ እንዳሉ እየተከታተሉ ዘገባዎችን ያቀርባሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ስርአተ ቀብሩ እስኪፈፀም ድረስ እንደሚቆይ ቢነገርም ከዛ በኋላም ምናልባት እንዳሁኑ ሙሉ የፕሮግራማቸውን ሰዓት ባይሆንም እስከተወሰነ ጊዜ በተመሳሳይ ሁኔታ ሊቀጥል እንደሚችል ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ጋዜጣና መፅሄቶችም ስለመለስ በሚያወሩ ፅሁፎች እንዲሁም ከተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የተላኩ የሃዘን መግለጫዎችን ከታዋቂ ሰዎች የተሰጠ አስተያየት ጋር ይዘው ወጥተዋል፡፡

ፌስቡክ መንደር ደግሞ ጠ/ሩ የመሞታቸው ዜና በአገር ውስጥ ሚዲያ እስከተነገረበት ሰዓት ድረስ አትሌቶቻችን በለንደን ኦሎምፒክ በተሳተፉበት ወቅት ስለተገኙት ውጤቶች ከተወራባቸው ውስን ቀናት ውጪ ለተከታታይ ስልሳ ቀናት ወሬው ሁሉ በአብዛኛው የመለስ የጤና ሁኔታ ነበር ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ የተለያዩ ምንጮችን በመጥቀስ መሞቱን ሲዘግቡ የነበሩ ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊ ሚዲያዎች ነበሩ፡፡በጠና መታመሙን እና ከዚህ በኋላ ብዙ ጊዜ እንደማይቆይ የሚያትቱ ወሬዎችን ያስነበቡን የውጪ ደህረ ገፆችም የነበሩ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ በአገር ውስጥ የሚገኙ ጋዜጦች በጣም እስክንገረም ድረስ እርስ በርሱ የሚጣረስ መረጃ ሲያቀርቡ ነበር፡፡ ከኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር የሚሰጡ መግለጫዎችም እንዲሁ ግልፅነት የጎደላቸው እና ሙሉ ምላሽ የሚሰጡን አይነት አልነበሩም፡፡ በስተመጨረሻም አቶ በረከት የመለስ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እና ለአዲስ አመት መጥተው እንኳን አደረሳችሁ እንደሚሉን ነግረውን ነበር የቆምነው፡፡

ሞቱ በአገራችን ሚዲያ እስከተነገረበትም እለት ድረስ በፌስቡክ እና በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች ያሉ ተሳታፊዎች ‹አልሞተም›፣ ‹ሞቷል› እና ‹በጠና ታሟል› ብለው ማሳመኛ የሚሉትን ሃሳቦች እያነሱ በንቃት ሲወያዩ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ከዚህም አልፈው ድህረ መለስ ትንታኔ ሲሰጡ እና የተለያዩ ግምቶቻቸውን ሲያካፍሉም ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የመለስ ሞት በአገራችን ሚዲያ አብዛኛው ሰው ባልጠበቀበት ሰዓት ሲገለፅ ውይይቱ በመለስ ሞት ማዘንን እና አለማዘንን በመግለፅ ተቀየረ፡፡ ያዘኑት ያላዘኑትን ባለማዘናቸው፤ ያላዘኑቱ ደግሞ ያዘኑትን በማዘናቸው መውቀስና መተቸት ተጀመረ፡፡እስካሁንም ድረስ ይህ መወቃቀስ አላቆመም፡፡ በበኩሌ ‹ማዘን› ወይም ‹አለማዘን› ከውስጥ የሚመነጭ ስሜት እስከሆነ ድረስ ባለመስማማት መለያየት ሲቻል ‹ማዘን ነበረብህ› ወይም ‹ማዘን አልነበረብህም› ብሎ መፍረድ እና ያልተገቡ ቃላትን መወራወር ትክክል አይመስለኝም፡፡ ደግሞም ማዘንም ያለማዘንም የግለሰብ መብት እና ምርጫ ናቸው እንጂ ግዴታ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በፌስቡክ በምናያቸው ውይይቶች ላይ የሚስተዋሉት ወቀሳዎችና ትችቶች ግፋ ቢል ስድብ ቢታከልባቸው ነው፡፡ በርግጥ እኛ ሳናቅ በስውር የተፈፀሙ ወይም የሚፈፀሙ ከስድብ የዘለሉ ነገሮች ተከስተውም ሊሆን ይችላል፡፡ በማረሚያ ቤቶችና በአንዳንድ ቦታዎች ግን ነገሩ አለአግባብ ተካብዶና ትኩረት ተሰጥቶት እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ነገሮች እየሰማን ነው፡፡

Monday, August 20, 2012

ዳኛቸውና ገዢ ሐሳቦቹ

እንዳልካቸው ኃ/ሚካኤል እና አቤል ዋበላ

ከዶ/ር ዳኛቸው ጽሁች መሀከል ጥቂቶቹ

የቄሳር እና አብዮት መጽሐፍ ዳሰሳ
አንዲት ኢትዮጵያ ሬድዮ
ግልጽ ደብዳቤ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ
ግልጽ ደብዳቤ ለአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት  አዲስ ጉዳይ መጽሔት
ሰብል እርሻ በጅብ ማረሻ  ፍትሕ ጋዜጣ
ዳኛቸው ስለ ብርቱካን   አዲስ ነገር ጋዜጣ

ብሔራታ ወልማታ- ሸገር ራዲዮ ጋር ያደረው ቃለ ምልልስ
የአገራችንን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስፋት እና ጥልቀት ስናስተውል ብዙዎቻችንን በቀቢጸ ተስፋ እንባክናለን፡፡ ይህን ለማሻሻል የተጀመረ ተዋስኦ አለመኖሩ ደግሞ ሀዘናችንን እጅግ ያበረታዋል፡፡ በተማሩትና በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ ዙሪያ እንኳን ትንፍሽ የማይሉ ነገር ግን ማዕረጋቸው ላጠራር የከበደ ሰዎች በየመስኩ ተደርድረዋል፡፡ብዙዎቹ ልሂቃን ትውልድን በሚገራና አቅጣጫ በሚያሳይ መልኩ አርአያ አለመሆናቸው አገሪቱ  በሐሳብ ክፍተት እንድትዳክር አድርጓታል፡፡ ዞን ዘጠኝም የነገዋ ኢትየጵያ መጻዒ ተስፋ የሚያሳስባቸው ወጣቶች ስብስብ እንደመሆኑ መጠን የራስንም የአቻንም መደናበርን ለመቀነስ ወይም ሐሰሳን ለመደገፍ ስናስብ አገሪቱ ካሏት ጥቂት የአደባባይ ምሁራን አንዱ የሆነው ዶ/ር ዳኛቸው አሠፋ ላይ አይናችን አረፈ፡፡ (በዚህ ጽሑፍ ላይ እኚህን የተከበሩ ምሁር ‹አንቱ› ሳንል የቀረነው፣ ለንባቡ ቅልጥፍና እንዲመች በማሰብ መሆኑን አንባቢዎች እንድታውቁልን፡፡)

ከዚህ በፊት ለአደባባይ የዋሉት ሥራዎቹ እጅግ ቢማርኩንም ወጥ የሆኑ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ይህንን የሐሳብ ኦና (idea vacuum) ለመሙላት ከሚታትር መምህር  የበለጠ ለመቅሰም በአንድ ወዳጃችን እርዳታ አገኘነው፡፡የዳኛቸው ሐሳቦች እጅግ የሚገዙ ለአብዛኛው ሰው ቅርብ የሆኑና በቀላሉ በሚገቡ ናቸው፡፡ ሀገራዊ ስነ ቃሎችና ስነጽሑፎችን በማጣቀስ፣ የሀገራችንን የቅርብና የሩቅ ታሪኮች ከፍልስፍና ንድፈ ሐሳብ ጋር በማጣመር  የመተንተን አቅም አለው፡፡ ይህንን ታላቅ ምሁር ከአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ውጭ ላለው የህብረተሰብ ክፍል በማስተዋወቅ አዲስ ነገር ጋዜጣ ጉልህ ሚና ተጫውታለች፡፡ በወቅቱ በእስር ቤት የነበረችውን የአእምሮ እስረኛ ዘሪ ብርቱካን ሚደቅሳን እስራት ኢፍትሕዊነት አስመልክቶ በጻፋቸው ተከታታይ ሑፎች ወደ አደባባይ ብቅ ያለው ዶ/ር ዳኛቸው በብዙ አካዳሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙርያ ገዢ ሐሳቦችን እያካፈለ ይገኛል፡፡እኛም ከነዚህ ብዙ ጉዳዮች ውስጥ የተወሰኑትን  በመምረጥ ትውልድ ሊያተኩርባቸው እና የምር ሊያነባቸው እና ሊያዳምጣቸው የሚገ መሆናውን ለመጠቆም እንዲህ አቅርበነዋል፡፡  


የአደባባይ ተዋስኦ /public discourse/

ዶ/ር ዳኛቸው የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብር ከተፈለገ ጫፍ አልባ ውይይት (endless conversation) ያስፈልጋል ይላል፡፡ በንግግር ተዋስኦ የሚመጣው ችግር በበለጠ ንግግር ማሸነፍ ይገባል ሲልም ይከራከራል፡፡ አንዳንዶች ያለገደብ ውይይትን መፍቀድ  ለብዙ የምግባር ችግሮች (ዘለፋ፣ ስድብ እና ልቅ ወሲብ ቀስቃሽ ምርቶች ለመሳሰሉት..) ይዳርጋል ይላሉ፡፡ እነዚህ ችግሮች መኖራቸው አይካድም፡፡ ይህ ግን እቀባ/ እግድ በመጣል  ሊፈታ አይችልም፡፡ ከነጻ ንግግር የሚመጣን ችግር ለመፍታት የበለጠ ነጻ ንግግር (more free speech) መፍቀድ ይገባል፡፡ ብሔርን ብሔርን ያጋጫል፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ያላትማል የሚል ሰባራ ሰንጣራ ምክንያት በመት ነጻ ንግግርን/ማሰብን ለማለፍ ወይ ለማገድ መሞከር ተገቢ አይደለም ይላል፡፡ የውይይት ባህል መዳበር እንዳለበት ሲያሰረዳ ደግሞ አውሮጳውያን የዲሞክራሲ ባህል ጉዞን ሲጀምሩ በዘመነ አብርኆት (enlightenment) ወደ አንድ ክፍለ ዘመን ለሚጠጋ ጊዜ የነበውን ወግ እና ባህል ፈትሸዋል፡፡ ሰፋ ያለ የውይይት ዘመንን በማለፍ ከዲሞክራሲ ባህል ጋር ተለማምዋል ከዲሞክራሲ አሰራር ጋር የሚጣረሱ ግባራትን እና ጽንሰ ሳቦችን ሁሉ ለማጥራት ችለዋል ይለናል፡፡

Sunday, August 19, 2012

ጋዜጦች እና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ (አሥራአንድ)


(ከነሐሴ 7 እስከ ነሐሴ 14፤ 2004)

የኛ ፕሬስ ጋዜጣ ሲፒጄ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት አዘጋጅ የሱፍ ጌታቸው ይፈታ ማለቱን እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ድንጋይ ይጥረቡ መባሉ እንዳሳዘናቸው ዘግቧል፡፡

ፍኖተ ነፃነት በቃለ መጠይቅ አምዱ (/) ክቡር ገናን ይዞ ወጥቷል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ተግዳሮቶች እና እንቅስቃሴዎች አወያይቶዋቸዋል፡፡ አቶ ክቡር ገናም ‹አንድ ህዝብ ዝም ብሎ ተኝቶ ሲረገጥ አይውልም፤ ድንገት ይነሳል› ማለታቸውን በፊት ገጹ አስፍሯል፡፡

በዚህ ሳምንት አቶ ክቡር ገና ከሰንደቅ ጋዜጣም ጋር ቆይታ ነበራቸው፡፡ በተመሳሳይ የሲቪል ማህበራት ጉዳዮች ዙሪያ ለሰንደቅ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል፡፡

የጠ/ መለስ ነገር
ከፓትሪያርኩ ዜና እረፍት በፊት የወጡት ጋዜጦች  ሁሉም በፊት ገጻቸው የጠ/ሚኒስትሩን መጥፋት ሽፋን ሰጥተውታል፡፡

የኛ ፕሬስ በፊት ገጹ የጠ/ሚኒስተር መለስ ጉዳይ እያወዛገበ ነው ሲል የተለያዩ ተቋማት ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጡትን ዘገባ አስነብቧል፡፡

መለስ ወደ ስልጣናቸው አይመለሱም - ዘጋርዲያን
ከአዲስ አመት በፊት ስራቸውን ይጀምራሉ - አቶ በረከት
የጠ/ሚሩ የግል ተተኪ አለመኖር አሳስቦናል - የኬንያው /ሚኒስተር
ከታቦ ኢንቤኪ ጋር በጉዳዩ እተማከሩ ነው - ፋይናንሺያል ታይምስ
ከአሁኑ ስልጣን ለመያዝ እርስበርስ እየተሻኮቱ ነው - ሀይሉ ሻውል