Saturday, July 21, 2012

የመለስ ዜናዊ ፲ ታላላቅ የአፍ ወለምታዎች


የዞን ዘጠኝ ነዋሪዎች የሆኑት በፈቃዱ ዘ ኃይሉ የመለስ ዜናዊ ‘ሀሁ’ በስልጣን ጎዳና እንዲሁም ዘላለም ክብረት መለስ ወደ ውጭ - መለስ ከውጭ በሚል ርዕስ ሁለት ጦማሮች አስነብበውናል፡፡ ይህም ስለጠቅላያችን የጤና ሁኔታ ከነበረው ውዝግብ መለስ ብለን ሌሎች ሁኔታዎች እንድንቃኝ ዕድል ሰጥቶናል ፡፡ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ ነው፤ እሰኪትንሽ ቅዳሜ ቅዳሜ የሚሸት ነገር እያወራን ዘና እንበል በሚል ደግሞ ይችን ጽሑፍ ከዱራሜ ዶት ኮም ያገኘነውን የጠቅላያችንን አስር ታላላቅ የአፍ ወለምታዎች ፣ በዚህ ንግግራቸው የተገረመው አብዛኛው ሰው ወደሚሰማው ቋንቋ እንደወረደ ተርጉመን ለአደባባይ አውለነዋል፡፡


፲. በ1983  ዓ.ም. በለንደኑ ጉባዔ  በኢህአዴግ ታርጋ የተሰባሰቡት ቡድኖች የፓርቲያቸው ህወሓት ተቀጥላ እንደሚሆኑ ለአሜሪካና ብሪታኒያ ባለስልጣናት አረዷቸው፡፡ብሪታኒያውያኑ ይህንን በተቃወሙ ጊዜ ቁጣቸው በግልጽ የሚታየው አቶ መለስ እንዲህ አሉ፡፡

     “አንድ ነገር ግልጽ ላድርግ  ፤ ከጉባዔው በኋላ  ኢህአዴግ የሚባል መንግስት አይኖረንም፡፡”

           
፱.  በ1985/6  ዓ.ም. ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸውን እይታ በአንድ ቃለ መጠይቅ ማብቂያ ላይ እንዲያካፍሉ ከአንድ ዘጋቢ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ መለስ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡፡

     “የኢትዮጵያ ዕድሜ መቶ አመት ብቻ ነው ፤ከዚህ በቀር ሌላ  የሚያወሩት ራሳቸውን በተረት ተረት እያሞኙ ነው፡፡" 

፰. በ1986/7 ዓ.ም. አስመራ ከተማ ውስጥ  ለአንድ የውጭ ሀገር ጋዜጠኛ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ስለ ኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

    “ከኢሳይያስ ጋር አንድ ሰዓት ማሳለፍ፣ 10 መጽሐፍ ከማንበብ በላይ ልበብሩህ፣ አዋቂ እና ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡”

፯. ለአምስት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያን ታሪክ ካጠኑት ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ጋር በ1989 ዓ.ም.  በነበራቸው ወይይት ከምንሊክ ወረራ በፊት ኢትዮጵያ የምትባል አንዲት  አገር እንዳልነበረች ተናገሩ፡፡ይህ የበለጠ አጽንኦት ለመስጠት ሲሞክሩ እንዲህ አሉ፡፡

      “ትግሬዎች የአክሱም  አላቸው ፤ ይህ ለጉራጌ ምኑ ነው? አገዎች ላሊበላ  አላቸው ፤ ይህ ለኦሮሞ ምኑ ነው? ጎንደሬዎች ቤተ መንግስት አላቸው፤ ይህ ለወላይታ ምኑ ነው?”

፮. ለመንግስት ሚዲያዎች በሰጡት አንድ ቃለ መጠይቅ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከጨርቅነት የዘለለ ምንም እንዳልሆነ ተናገረዋል፡፡

      “ባንዲራ የጨርቅ ቁራጭ ነው”

፭. በ1990 ዓ.ም. ሰማኒያ ሺ የሚደርሱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ኤርትራውያንን ሀብት ንብረታቸውን ቀምተው  ኢ-ሰብዐዊ በሆነ መልኩ ከሀገር ካስወጡ በኃላ ለፓርላማው እንዲህ አሉ፡፡

      “የአይናቸው ቀለም ካላማረን ፣ ከሀገራችን የማባረር መብት አለን፡፡”

፬. በ1993 ዓ.ም. ልጇ ወደ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዘምቶ አለመመለሱ ያሳሰባት  እናት ልጇ ወዴት እንዳለ መለስ ዜናዊን  አጥብቃ ጠየቀች፡፡በጥያቄዋ ድምጸት የተበሳጩት አቶ መለስ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡፡

      “ሴትዮ፣ ልጅሽ በስድስት ወራት  ወደቤቱ ካልተመለሰ ፣ መልሱን ታውቂዋለሽ፡፡”

፫. በ1997 ዓ.ም. ምርጫን ተከትሎ በተካሄደው  ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ  በጠቅላያችን ትዕዛዝ 193 ያልታጠቁ ንጹሐን ዜጎች በአዲስ አበባ እንዲገደሉ ትዕዛዝ  ሲሠጡ የትግራዋይ ተወላጅ ለሆነው ለታማኛቸው ጄኔራል ሳሞራ አማራዎችን ለማለት አህዮች የሚለውን ቃል ተጠቅሟል፡፡

      “እነዚህ አህያ አማራዎች  ትምህርት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሰላማዊና  ሃይማኖተኛ  የሚሆኑት ክላሽንኮቭ ስትደግንባቸው ብቻ ነው፡፡”

፪. ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ የከሸፈ ፣ ተከተታይ ወረራ   በ1998 ዓ.ም.  በሱማሊያ መሬት ላይ መሬት ያዛ በነበረበት ሰዓት ለ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አላማቸው የኢስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረትን ለማንበርከክ ሳይሆን በዚያ የሌሉትን በሱማሊያ የሚገኙት የኤርትራ ወታደሮች ለማሰደድ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

     “እያጠቃን ያለነው   በሱማሌ ወይዛዝርት ቀሚስ ስር  የተሸሸጉ የኤርትራ ኃይሎችን ብቻ ነው፡፡”


፩. በ2002 ዓ.ም. ከሊቢያው አምባገነን ሙዐመር ጋዳፊ ጋር ስለ ሁለትዮሽ ግንኙነት በሚወያዩበት ጊዜ አቶ መለስ እንዲህ አሉ፡፡

       “እኔ የመናዊ ነኝ ፤ የመናዊ እንደሆንኩኝ አውቃለው ፤ ሁላችንም የመናውያን ነን፡፡ ከነገሥታቱ  ቤተሰብ በቀር ሁላችንም አረብ ነን፡፡”